March 16, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በተፈጠረው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ

ማሻ፤ መጋቢት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን በአደጋው የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ለፕሬዝዳንት ታዬ አፀቀስላሴ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በትስስር ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ  በመልዕክታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ከልብ የመነጨ የመጽናናትና የድጋፍ መልዕክታቸው ለህዝቡ እንዲደርስ ጠይቀዋል።

በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።