ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ፣ የመልካም አስተዳደር ማስፈኛና በመንግስት አሰራር ውስጥ የህዝብ ተሳትፎ የሚረጋገጥባቸው ተቋማት መሆናቸው ተገለጸ።
በሸካ ዞን የማሻ ወረዳ ም/ቤት በ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤው የ2018 የ6 ወራት አፈጻጸም መድረክ አካሂዷል።
በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ሁሉ አቀፍ የልማት ስራ አፈጻጸም ዝርዝር ተግባራትን የማሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን አዳሾ ለምክር ቤቱ አባላት ሪፖርት አቀርበዋል።
በግብርናው ዘርፍ ወረዳው ካለው የመልማት አቅም አንጻር ዘርፈ ብዙ ዕቅድ በማቀድና ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በመኸር፣በጥራጥሬ፣ በአትክልት፣ በስራ ስር፣ በፍራፍሬ፣ በቡና ሻይ ቅመማ ቅመም፣ በመስኖ፣ በህብረት ስራና በተፈጥሮ ደን ጥበቃ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ተናግረዋል።
በወረዳው ገቢ አሰባሰብ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪ ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ስነጻጸር በእጥፍ ማደጉን ለምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።
በጤና ስራ ዋናው ተግባር ቅድመ መከላከልና አክሞ ማዳን በመሆኑ ጤንነቱ የተጠበቀ ህብረተሰብ በመፍጠር አምራች ዜጋ ለማድረግ እንደ ወረዳ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት።
እንደ ሀገር ለትምህርት በተሰጠው ልዩ ትኩርት ህዝቡን ያሳተፈ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ከማከናወን ረገድ ከመንግስት ጎን በመሆን ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና በተሻለ ደረጃ እንደሚገኝ ዋና አስተዳዳሪ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
በሴቶች ህጻናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ከተጠቃሚነታቸውና ደህንነታቸውን ከመጠበቅ አንጻር በየዘርፉ ሰፊ ዕቅድ ታቅዶ በመከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል።
ከህግ ፍትህ መልካም አስተዳደር ዘርፎች አንጻር አሰራሩን በተከተለ መልኩ የተለያዩ ወሳኔዎችና የስራ አቅጣጫዎች ጭምር በመስጠት ለህዝቦች ተጠቃሚነት እንደየ ስራ ዘርፍ ተፈጻሚነት እያገኘ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪ ገልጸዋል።
በሪፖርቱ መነሻ የምክር ቤቱ አባላት በሰጡት አስተያየት በግብርናው፣ በትምህርት፣በጤና፣በገቢ፣በጸጥታና በትራንስፖርት ዘርፍ የተከናወነስራና የአርሶ አደሩ የግብዓት አጠቃቀም ፍላጎት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው ቡናን በወቅቱ ለማዕከላዊ ገበያ ከመላክ፤ ገበያን ለማረጋጋት በአትክልትና መሰል ዘርፎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ተናግረዋል።
በአካባቢው በአርሶ አደሩ የሚመረቱ የግብርና ምርቶች የተለያዩ ደላሎች በሚፈጥሩት ሴራ አርሶ አደሩ እየተበዘበዘ በመሆኑ ዘርፉን ፈትሾ ማስተካከል ያስፈልጋልም ብለዋል።
ዘጋቢ: ካሳሁን ደንበሎ
በሸካ ዞን የማሻ ወረዳ ም/ቤት በ4ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤው የ2018 የ6 ወራት አፈጻጸም መድረክ አካሂዷል።
More Stories
በመካከለኛው ምሥራቅ የተባባሰው ጦርነት ከተለኮሶ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ያዘ።
ታሪካዊ ስህተትን የማረም ጉዞ …
ኤች አይ ቪ ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር በዜጎች ማህበራዊ ሕይወት ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር በማድረግ ክልላዊና ሀገራዊ ግቦችን ማሳካት እንደሚገባ ተገለፀ ።