February 26, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ  ምርጫ ማኒፈስቶና የምርጫ ምልክት ትዉዉቅ መድረክ

ማሻ፤ የካቲት 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ  በዞኑ ቴፒ ከተማ የ7ኛዉ ሀገራዊ  ጠቅላላ ምርጫ ማኒፈስቶና የምርጫ ምልክት ትዉዉቅ መድረክ በዞኑ ቴፒ ከተማ የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ አባላትና  የፓርቲዉ  ደጋፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል ።


‎በመድረኩ የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ  ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለማየሁ ዓለሙ እንደገለጹት ኢትዮጵያ  ብዙ እምቅ አቅም ያላት ሀገር ብትሆንም በርካታ መሠራት ያለባቸዉ ጉዳዮች መኖራቸዉን አንስተዋል።

‎በዚህም ህብረ ብሔራዊነትን ለማጽናት፣ድህነትና ኋላ ቀርነትን ለመቅረፍ፣ የዉስጥና የዉጭ ግጭትና ጦርነትን ለማስቀረት ብሎም ሌሎችንም ችግሮች ለመቅረፍ  የብልጽግና ፓርቲ ይሠራል ብለዋል።

‎የኢትዮጵያን የባህር በሯን ለማስመለስና ሌሎችንም ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ  እየተሠራ ነዉም ብለዋል።

‎የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ኢትዮጵያ ብዙ ተስፋ ያላት የብዙ ታሪክ ባለቤትና ዕድሜ ጠገብ ሀገር መሆኗን አንስተው ሁሉም ዜጎች እኩል የሚጓዙበት ብሔራዊ ራዕይ እንዲኖር ፓርቲያቸዉ እንደሚሠራም ተናግረዋል።

‎በሰላም   ረገድ  በተሰራዉ ትልቅ ተግባር ዛሬ ላይ ሸካ ዞን በሰፊዉ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እየሆነ እንዳለ አንስተዋል።

‎ቀጣይነት ያለዉ ግዙፍ የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ፓርቲዉ እንደ ሀገር እየሠራ እንዳለም አቶ አበበ ማሞ አስታዉሰዋል።

‎የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ሰፊ ርብርቦች እየተደረገ እንዳለ ተናግረዋል።

‎የፓርቲያቸዉ  ምልክቱም የስንዴ ነዶ መሆኑንና   ምልክቱም የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።