February 26, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አሜሪካ እና ኢራን ግጭትን ሊያስቀር ይችላል የተባለውን ወሳኝ ውይይት ዛሬ ይጀምራሉ

ማሻ፤ የካቲት 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ሊሰነዝር የዛተውን ጥቃት ሊያስቀር ይችላል የተባለ የመጨረሻ ዙር የዲፕሎማሲ ንግግር ነው ሐሙስ በስዊትዘርላንድ ይካሄዳል የተባለው።

ይህ ሦስተኛ ዙር ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ከፍተኛ ወታደራዊ ውጥረት ለማርገብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ለመግታት የኒውክሌር ስምምነት ላይ ካልተደረሰ የተመጠነ” ወታደራዊ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

ኢራን በበኩሏ ለማንኛውም ጥቃት ምላሽ እንደምትሰጥ በመግለጽ ላይ ትገኛለች።

ያም ሆኖ በኦማን አደራዳሪነት በሚካሄደው በዚህ ንግግር፣ የኢራንን ልዑክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ የሚመሩ ሲሆን፣ የአሜሪካን ወገን ደግሞ የፕሬዝዳንቱ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር ይወክላሉ።

ውይይቱ የሚካሄደው አሜሪካ ከ2003 የኢራቅ ወረራ በኋላ ከፍተኛ የተባለውን ወታደራዊ ኃይል፣ የጦር መርከቦችና አውሮፕላኖችን በመካከለኛው ምሥራቅ ባሰማራችበት ወቅት ነው።

ውይይቱ ክልላዊ ጦርነትን ለመከላከል እንደ የመጨረሻ ዕድል ቢታይም፣ በሁለቱ አገራት መካከል ባለው ጥልቅ አለመተማመን ምክንያት ስምምነት ላይ የመድረሱ ዕድል አሁንም አጠራጣሪ እንደሆነ ቀጥሏል።

ዘገባው የቢቢሲ ነው

የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

አሜሪካ እና ኢራን ግጭትን ሊያስቀር ይችላል የተባለውን ወሳኝ ውይይት ዛሬ ይጀምራሉ

የካቲት 19፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ሊሰነዝር የዛተውን ጥቃት ሊያስቀር ይችላል የተባለ የመጨረሻ ዙር የዲፕሎማሲ ንግግር ነው ሐሙስ በስዊትዘርላንድ ይካሄዳል የተባለው።