ማሻ፤ የካቲት 17/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በጃፓኗ ኦሳካ ከተማ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ 3.6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ 29 ጥፍጥፍ ወርቆችን ለከተማዋ አስተዳደር በስጦታ አበረከተ።
ጥፍጥፍ ወርቁ በሁለት ሳጥኖች ተደርጎ በከተማዋ አስተዳደር ቢሮ አቅራቢያ በድንገት የተገኘ ሲሆን፣ ለጋሹ ከወርቅ ሳጥኖቹ ጋር ባስቀመጠው አጭር ማስታወሻ፤ ስጦታው በከተማዋ ውስጥ ለሚያረጁ የንጹህ ውኃ ቧንቧዎች ጥገናና ለሕዝብ አገልግሎቶች እንዲውል ፍላጎቱ መሆኑን ገልጿል።
ከተማዋ ለቧንቧዎች ቅያሬ ከፍተኛ በጀት በሚያስፈልጋት ወቅት የተገኘው ይህ ድንገተኛ ስጦታ “የሰማይ ሲሳይ” ተብሏል።
ማንነቱን መግለጽ ያልፈለገው ይህ ግለሰብ ምንም ዓይነት አድራሻም ሆነ ምልክት ያላስቀመጠ ሲሆን፣ የከተማዋ ከንቲባ ለለጋሹ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
More Stories
የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት ዳግም ያረጋገጡ አዲስ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች…
በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት የበልግ ተጠቃሚ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ ተባለ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ከኢራን ጋር ድርድር ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ