February 15, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክልሉ ታዳጊዎች በውድድሩ የሰበሰቧቸው 13 ሜዳሊያዎች በምን የስፖርት አይነት የተገኙ ናቸው?

ማሻ፤ የካቲት 8/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ ለ8 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ተጠናቋል።

‎እንደሀገር በ15 ስፖርት አይነቶች በተካሄደ ውድድሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ120 በላይ ስፖርተኞችን በመያዝ በ9 የስፖርት አይነቶች ተወዳድሮ በአጠቀላይ በቁጥር 13 ሜዳልያዎችን መሰብሰብ ችሏል።

ታዲያ እነዚህ ሜዳሊያዎች በምን የስፖርት አይነት የተመዘገቡ ናቸው?

•‎ጂምናስቲክ ውድድር በቡድን በወንዶችና በሴቶች ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ 2 የነሐስ ሜዳልያዎች፤

•‎በፓራ-ሊምፒክ ስፖርት ውድድር በተለያዩ ዲሲፕሊን በሁለቱም ፆታዎች 2 የብር ሜዳልያ እና 3 የነሐስ ሜዳልያ በድምሩ 5 ሜዳልያዎች፤

•‎በጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር በወንዶች በቡድንና በነጠላ 3ኛ ደረጃ በመያዝ 2 የነሐስ ሜዳልያዎችን፤

•‎የአትሌቲክስ ስፖርት ውድድር አካል በሆነው በሴቶች ጦር ውርወራ 3ኛ ደረጃ በመያዝ የነሐስ ሜዳልያ፤

•‎በቡድን ሴቶች የወለል ተግባር ሌጣ ፈረስ እና በወንዶች የወለል ተግባር ሌጣ ፈረስና የትይዩ ጥንድ አግዳሚ ውድድር 3ኛ ደረጃ በመያዝ 2 የነሐስ ሜዳልያ፤

•በእግርኳስ ውድድር ምንም ጨዋታ ባለመሸነፍ የፍጻሜ መድረስ ሲቻል በዚህም የብር ሜዳሊያ፤