February 11, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ስፖርታዊ ውድድር በዜጎች መካከል ማህበራዊ ትስስርና አንድነት በማጠናከር ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሚናው የጎላ መሆኑን የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡

ማሻ፤ የካቲት 4/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር “የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ”በሚል መሪ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በውድድሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የታዳጊዎች እግር ኳስ ድል ቀንቶታል።

‌‎ ‎ውድድሩ እንደአገር በ15 የስፖርት አይነቶች እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል  ስፖርት ልዑካን ቡድን በዘጠኝ ስፖርት አይነቶች ከ120 በላይ ልዑካን ቡድኖች እያሳተፈ የሚገኝ ሲሆን በውድድሩም  ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።

‌‌‎በእግር ኳስ ውድድር ምድብ ‘ለ’  ላይ ከአማራ እና ሶማሊያ ክልሎች ጋር የተደለደለው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ‎የመጀመሪያ ቀን ምድብ ጨዋታውን ከአማራ ብሔራዊ ክልል ጋራ ያደረጉ ሲሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አቻቸውን አማራ ብሔራዊ ክልልን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በተመሳሳይም በትላንትናው ቀን በተካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ድል የቀነው ሲሆን  ሶማሊያ ክልል ቡድንን 4ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አልፈዋል።

ሌለኛው ትላንት በተካሄደው ‎በፓራሊምፒክ አትሌቲክስና አሎሎ ውርወራ የፍፃሜ ውድድር ላይ ውጤቶች ተመዝግቧል።

በዚህም ውድድር የ‎ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በፖራሊምፒክ ውድድር የእግር ጉዳት ክላስ-ቢ አሎሎ ውርወራ በሴቶች የብር ሜዳሊያ እና የእጅ ጉዳት በወንዶች 100 ሜትር የነሀስ ሜዳልያ መሰብሰብ ተችሏል።

‎በምዘናው መድረክ ላይ የተገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ዳዊት ደስታ ስፖርት በውድድር መድረኮች ስፖርተኞችን ከማወዳደር ባሻገር በዜጎች መካከል ማህበራዊ ትስስርና አንድነት እንዲጎለበት በማድረግ ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሚናው የጎላ መሆኑ ገልጸዋል።

‎ውድድሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ13-15 ዓመት ዕድሜ ክልል ባሉ ታዳጊ ወጣቶች መካከል የሚካሄድ ሲሆን መንግስት ታዳጊ ስፖርተኞችን ለማፍራት በዕድሜ ዙሪያ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ማሳያ ነው ሲሉም አቶ ዳዊት ተናግረዋል።

‎ስፖርት ከአካላዊ ብቃትና ጥንካሬ ባለፈ የማህበረሰብን ስነ-ልቦና በመገንባት ብቁና አሸናፊ ዜጋ እንዲፈጠር ከፍተኛ ድርሻ የሚጫወት ዘርፍ መሆኑን ያወሱት አቶ ዳዊት ለዚሁም በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ያለው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ሚናው የላቀ መሆኑን አቶ ዳዊት ደስታ አብራርተዋል።

‌‎በምዘና ውድድሩ ክልሉን ወክለው በዘጠኝ ስፖርት አይነቶች ከ120 በላይ ልዑካን ቡድኖች እየተሳተፉ እንደሚገኙ አቶ ዳዊት ደስታ ጠቁመዋል። ዘገባው የክልሉ መ/ኮ ነው።