ማሻ፤ የካቲት 3/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ከየካቲት 4 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚከበረዉ የማጃንግ ብሔረሰብ ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውተገልጿል ።
የበዓሉን ቅደመ ዝግጅት ስራዎች በማስመልከት መግለጫ የሰጡት የማጃንግ ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም ሰብሳቢ አቶ ዮሐንስ በንዲ እንደገለጹት ከየካቲት 4 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ለሚከበረዉ የማጃንግ ብሔረሰብ ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገለጸዋል ።
የበዓሉ መከበር የብሔረሰብን ባህል፣ታሪክ፣እና ቋንቋን ከማሳደግ ባለፈ ለልማት እና ለሰላም ዕሰት ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ይህንኑ ይበልጥ ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል ።
ለረጅም ዓመታት ተዘንግተው የቆዩ የማጃንግ ብሔረሰብ ባህላዊ እሴቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን እንደገና ለማነቃቃት ያለመ ሲምፖዚየም መሆኑንም ጭምር አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል ።
ከየካቲት 4 እስከ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሚከበረዉ የማጃንግ ብሔረሰብ ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም ላይ የባህል ትርኢቶች ፣ የምግብ አውደ ርዕይን ጨምሮ የማጃንግ ቋንቋና ባህልን የሚዳስሱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይቶች እንደሚደረጉ ጠቁመዋል ።
በሲምፖዚየሙ ላይ ከጋምቤላ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቡ ተወላጆችና ተጋባዥ እንግዶች ፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ጨምሮ ፣የሌሎች ብሔረሰቦች ተወካዮች እንደሚሳተፉ ተገልጿል
More Stories
የአፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚ መሆን…
በዓለም ላይ ከፍተኛ ቀውስ እያስከተለ በሚገኘው ጦርነት እስካሁን ምን ተከሰተ?
ኢራን “እራሴን ለመከላከል የምፈጽመውን ጥቃት አጠናክሬ እቀጥላለሁ” አለች