ማሻ፤ የካቲት 3/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8)የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልልና የኮንታ ዞን አመራሮች የአመያ ከተማ የኮሪደር ልማት ፣የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል።
ክልሉ ተከማችተው የነበሩ ዕዳዎችን በማቅላል ወደ ምንዳነት በማሸጋገር በርካታ የልማት ስራዎችን በማስመረቅና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የመሰረት ድንጋይ በመስቀመጥ የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል።
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)የጪዳ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅን ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት ፍጥነትና ጥራትን ማዕከል በማድረግ ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ አስገንዝበዋል።
በግንባታው ሂደት የታዩ ችግሮችን ነቅሶ በመለየት ለችግሮቹ መፍትሔ አካል በመሆን ግንባታው አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በትጋት መስራት ይጠበቃል ብለዋል። ዘገባው የክልሉ መ/ኮ ነው
More Stories
የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለ39ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ አዲስ አበባ እየገቡ ነው
የብሔረሰቦችን ቋንቋ፣ ባህል እና መልካም ዕሴቶች እንዲጎለብቱ ማድረግ ለልማትና ለሰላም ዕሴት ግንባታ ያለው ፍይዳ የጎላ ነው ተባለ
ውስጣዊ ሰላምን ማፅናት፦ ወቅቱ የሚጠይቀው አርበኝነት