ማሻ፤ የካቲት 3/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ምሽት 5 ሰዓት 15 ላይ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል፡፡
በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው ማንቼስተር ዩናይትድ 5ኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
ወራጅ ቀጠና ላይ የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ በበኩሉ ተከታታይ ሁለተኛ ጨዋታውን ለማሸነፍ ይፋለማል።
ከእዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ምሽት 4 ሰዓት 30 ላይ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
በሊጉ ያለፉትን አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ያሸነፈው ቼልሲ አሸናፊነቱን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ቶተንሃም ሆትስፐር ከኒውካስል ዩናይትድ እንዲሁም ኤቨርተን ከቦርንማውዝ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት 30 ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
More Stories
የአርሰናል የድል ሰልፍ በለንደን ጎዳናዎች፤ ለታሪካዊው ቀን ቀጠሮ ተይዟል!
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የእግር ኳስ ጸሐፊዎች ማህበር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ
አርሰናል ከ20 ዓመት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ ደረሰ