ማሻ፣ ጥር 02/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ሴኔጋል ማሊን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ገብታለች።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሴኔጋል ኒጃይ ባስቆጠረው ግብ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በቅታለች።
በጨዋታው የማሊው ቢሱማ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
መርሐ ግብሩ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ አዘጋጇ ሞሮኮ እና ካሜሩን የሚያደርጉት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ይጠበቃል።
ሞሮኮ ታንዛኒያን በማሸነፍ እንዲሁም ካሜሩን ደቡብ አፍሪካን በማሸነፍ ነው ለሩብ ፍፃሜ የደረሱት።
More Stories
የ2026 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ …
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነቷ እንዲሰረዝ መወሰኑ አሳፋሪ ነው፡- የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኦጉስቲን ሴንግሆር
ቦርንማውዝ ከ ማንችስተር ዩናይትድ