ማሻ፣ ጥር 01/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በጥቃቱ አውዳሚ ነው የሚባለው ኦሬሽኒክ ሚሳኤል ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፥ የዩክሬን ቁልፍ ወታደራዊና መሰረተ ልማት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ሬውተርስ አስነብቧል።
በዚህም በፑቲን ላይ ተፈጽሟል ለተባለው ጥቃት ጥቅም ላይ የሚውሉ ድሮን ማምረቻዎች እና የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማት እንዲሁም የሃይል መሰረተ ልማቶች ኢላማ ተደርገዋል ነው የተባለው።
የኒውክሌር አረር መሸከም ይችላል የሚባለው ይህ ሚሳኤል ካለው ፍጥነት አንጻር ከተተኮሰ በኋላ ማምከን አስቸጋሪ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርም በጥቃቱ በርካታ ድሮኖችን እና ከፍተኛ አቅም ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች ማውደሙን ነው የገለጸው።
ባለፈው ታኅሣሥ ወር በፑቲን ላይ ተፈጽሟል ያለውን ጥቃት “የሽብር ድርጊት” ያለው ሚኒስቴሩ፥ ዩክሬን ለምትፈጽመው ጥቃት ከባድ አፀፋዊ ምላሽ ታገኛለች ሲልም አስጠንቅቋል።
ሬውተርስ
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …