ማሻ፣ ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የማርበርግ ቫይረስ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የሕይወት አድን መድኃኒቶችንና ክትባቶችን በድሮን የማድረስ ሥራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
የጤና ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በመተባበር ነው በድሮን የታገዘውን የክትባት ሥርጭት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሰነች ወረዳ ያስጀመሩት፡፡
መርሐ ግብሩ ሚኒስቴሩ የወረርሽኙን ሥርጭት ለመግታትና ራቅ ያሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ የወሰደው ፈጣን ምላሽ ርምጃ አካል ነው፡፡
በዚህ መሰረትም በዛሬው ዕለት በዳሰነች ወረዳ በድሮን የታገዘ የክትባት ሥርጭት በስኬት መከናወኑን ጤና ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
የዳሰነች ወረዳ ካለው ራቅ ያለ መልክዓ ምድር አኳያ በመኪና ለማጓጓዝ ረጅም ሰዓታት ይወስድ የነበረውን ጉዞ በድሮን በመታገዝ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ክትባቱን ማዳረስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
ይህም ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ወረርሽኞችን ቀድሞ የመከላከልና የመቆጣጠር አቅማቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገራቸውን በተግባር ያሳዩበት ነው።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ወረርሽኞችን ለመመከት የራሷን የውስጥ አቅም እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም መጀመሯን የሚያሳይ ትልቅ ተግባር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …