February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ አቻ ተለያዩ

ማሻ፣ ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሰንደርላንድ እና ሊድስ ዩናይትድ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ዛሬ 11፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሳይሞን አዲንግራ የሰንደርላንድን ግብ ሲያስቆጥር ካልቨርት ሉዊን የሊድስ ዩናይትድን ግብ ከመረብ አገናኝቷል።

የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 1:30 ላይ ክሪስታል ፓላስ እና ቶተንሃም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።