February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ደንብና መመሪያዎች ተፈጻሚነት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንሚገባ ተጠየቀ

ማሻ፣ ታህሳስ 18/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ከመልካ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በረቂቅ ደንብ፣ መመሪያዎች ላይ የባለድርሻ አካላት የግብዓት ማሰባሳቢያ የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ ምክክር በማድረግ ለግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች የተሰበሰበና ረቂቅ ደንብና መመሪያዎችቹ በቀጣይ ለመስተዳድር  ምክር ቤት  ቀርቦ በማጽደቅ ወደ ስራ የሚገባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በየጊዜው የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ተፈጻሚነቱ ውጤታማ ለማድረግ ቅንጂታዊ አሠራርን ማጠናከርና የህብረተሰብ ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚጠይቅ አንስተዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ፤ የቀረቡ ረቂቅ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና ጋይድላይንስ ጸድቆ ወደ ስራ ሲገባ ከዚህ ቀድሞ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ወቅት የሚታዩ ችግሮችን በእጅጉ እንደሚፈታ ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ደን፣ አከባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጂነር አስራት ገ/ማሪያም፤ የአካባቢና ማህበራዊ ተጽእኖ ግምገማ በተቀናጀ መልኩ ስራ ላይ ለማዋል ደንብና መመሪያዎች የህግ ተከባሪነትን በጠበቀ መልኩ መስራት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ  ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ዘገባው የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ነው።