የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ለአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።
“ባለፈው አንድ ዓመት እየሰራንባቸው የቆየነውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ውይይቶች በመቀጠል ፍሬያማ ውይይት አድርገናል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የሃሳብ ልውውጣችን የወል የቅድሚያ ጉዳዮቻችንን ለመከወን ብሎም ለጠንካራ ግንኙነት፣ ቀጠናዊ መረጋጋት እና ልማት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያፀና ነበር” ማለታቸው ተዘግቧል።
More Stories
ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ዕድገት ማነቆ የሚሆኑ ችግሮች ተለይተው በዘላቂነት መፈታት አለባቸው፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
አሜሪካ እና ኢራን ግጭትን ሊያስቀር ይችላል የተባለውን ወሳኝ ውይይት ዛሬ ይጀምራሉ
የመራጮች ዲጂታል ምዝገባ ሥርዓት ለምርጫ ተአማኒነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል – ምሁራን