ማሻ ፣ የሀምሌ 04፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ኮሚሽኑ በክልሉ 34 ወረዳዎች የአደጋ ስጋት እንዳለባቸው አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ለማ መሰለ በክልሉ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
በክልሉ 34 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ 269 ቀበሌዎች የአደጋ ስጋት ቀጠናዎች ተብለው መለየታቸውን አንስተዋል።
ከሰሞኑ በካፋ ዞን ጨና ወረዳ ኮዳ ቀበሌ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ290 በላይ ዜጎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።
ከዝናብ መጨመር ጋር ተያይዞ መሰል ጉዳት እንዳይደርስ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሰገንዝበዋል።
ጉዳቶችን ለመቀነስ በኮሚሽኑ የሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው ፤ አደጋው የደረሰበት ጨና ወረዳ ኮዳ ቀበሌ የምግብና የሰብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ በቂ ዝግጅት መኖሩን አስረድተዋል።
አደጋ የደረሰባቸውን ዜጎች በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት በየደረጃው ያሉ አካላት መደገፍ እንዳለባቸው ዶክተር ለማ አሳስበዋል።
አሁን ወቅቱ ዝናብ የሚበረታበት በመሆኑ ፤ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል ደሬቴድ ቦንጋ ቅርንጫፍ ዘግቧል።
More Stories
የሰው ተኮር ተግባራት በማጠናከር ሁለተናዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ገለፁ።
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል
በክልሉ ተደራሽነቱና ፍትሃዊቱ የተረጋገጠ የፍትሕ እና የዳኝነት ሥርዓት እንዲሰፊን የተጀመረው የትራንስፎርሜሽን ሥራዎች መጠናከር አለባቸዉ፦ክብርት ወ/ሮ ሃና አረአያስላሴ