September 16, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና በሚዛን-ቴፒና ቦንጋ የዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝደንቶች፣ ምክትል ፕሬዚደንቶች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት ተጀምሯል።

ማሻ ፣ የሀምሌ 01፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የሁለተኛው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተፈታኞች ፈተናቸውን በእንግሊዝኛ ትምህርት ዓይነት መጀመራቸውን ከዩኒቨርሲቲዎቹ መረጃ መወቅ ተችሏል።

የሁለቱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች ባስተላለፉት መልዕክት ለተማሪዎች መልካም ምኞታቸውን ገልጸው ፈተናውን ተረጋግተው መስራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

ፈተናው ከዛሬ ጀምረው ሶስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዚህኛውም ዙር የፈተና አሰጣጡ በወረቀት እና በበይነ-መረብ /Online/ እንደሚሰጥ ታውቋል።

ክልል ኮሚኒኬሽን