ማሻ ፣ የሰኔ 24፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የህንድ መከላከያ ሚኒስትር ራጅናዝሲንግ ከሩሲያ አቻቸው አንድረይ ቢሎሶቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ህንድ S-400 የተባለውን ሩሲያ ሰራሽ ተንቀሳቃሽ የሚሳኤል ስርዓት ከሩሲያ መግዛት በምትችልበት መንገድ ላይ ሚኒስትሮቹ መነጋገራቸውንም አርቲ ዘግቧል፡፡
የሚኒስትሮቹ ውይይቱ ከዚህ ቀደም የሀገራቱ መሪዎች በወታደራዊ ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ያደረጉት ምክክር አካል ነው ተብሏል፡፡
በዚህም ሩሲያ የአየር መቃወሚያ እና የተለያዩ ሚሳኤሎች ለህንድ ለማቅረብ እንዲሁም ሱ-30 የተባሉ የጦር አውሮፕላኖችን ስርዓት ማሻሻል ላይ ድጋፍ ለማድረግ እንደምትሰራ ቁርጠኛ ናት ተብሏል፡፡
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የአየርክልላችን ከጥቃት ለመከላከል S-400 የተባለዉሩሲያ ሰራሽ የሚሳኤል ስርዓት በስፋት ያስፈልገናልሲሉ ለፕረዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዚህ በፊትበአፅንኦት ነግረዋቸው እንደነበርም ዘገባው አመልክቷል፡፡
አሁን ላይ ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ዘርፍ እያደረጉት ያለው ትብብር በሁለቱ መሪዎች ውይይት እና ስምምነት ላይ መሰረት ያደረገ ነውም ተብሏል፡፡
ኢቢሲ
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ
ትራምፕ የቡድን 7 ጉባዔ ሳይጠናቀቅ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ