August 11, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሀገርቱ የሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎችን አስመረቁ

ሚዛን -ቴፒ ፣ ቦንጋ፣ አርሲ ፣ ወራቤ፣ ሐረማያ፣ ባህርዳር ፣ጅማ፣ ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ፣ደብረማርቆስ፣ አርባምንጭ፣አዲግራት፣ ጂንካ እና አሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል ።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በመደበኛ፣ በሳምንቱ መጨረሻ እና በማታ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸዉን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርስቲ በ2017 ዓ/ም በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት በቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎችን ማስመረቃቸውን በተለያዩ የሚዲያ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

በምረቃው መርሃግብር የክብር እንግዶች፤ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባላት፤ ሰኔት አባላት፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤ የሀይማኖት አባቶችና የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ዘገባዉ የክልል መንግስት ኮምንኬሽን ነዉ