ማሻ ፣ የሰኔ 14፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሌላ የኒውክሌር ሳይንቲስት መሞቱን፤ የኢራን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህም በእስራኤል የተገደሉ የኢራን ኒውክሌር ሳይንቲስቶችን ቁጥር 10 አድርሶታል።
ኢሳር ታባታቤይ የተባለው ተመራማሪ ሞት ይፋ የሆነው በቴህራን ሻሪፍ ዩኒቨርሲቲ ጋዜጣ ሲሆን፤ ኢሳር የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ ተማሪ ነበር ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ኢራን ቀደም ሲል ሌሎች ዘጠኝ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች መሞታቸውን ማረጋገጧ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ‘ቻናል 12’ የተባለው የእስራኤል ሚዲያ እስራኤል በኢራን በጀመረችው ዘመቻ፤ 9 የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቶችን በአንድ ጊዜ፤ እንዲሁም አሥረኛውን የኒውክሌር ሳይንቲስት በሌላ ጥቃት መግደሏን ዘግቧል።
ኢቢሲ
More Stories
እየተጠናከረ የመጣው የብሪክስ ሀገራት ግንኙነት…
አሜሪካ ሶሪያን አጠቃች
የሩሲያ ጦር በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ ተፈጽሟል ላለው ጥቃት አፀፋ በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።