August 1, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት አዲስ የተሾሙትን የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ መግደሉን አስታወቀ

ማሻ ፣ የሰኔ 10፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ እና ከአገዛዙ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑትን አሊ ሻድማኒ መገደሉን አስታውቋል።

ዋና አዛዡ የተገደሉት በማዕከላዊ ቴህራን በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ መሆኑም ተዘግቧል።

ጥቃቱ የተፈፀመው የእስራኤል ጦር በደረሰው መረጃ መሰረት፤ በኢራን ወታደራዊ ተዋረድ ውስጥ ካሉት ከፍተኛ ባለስልጣኖች አንዱ የሆኑትን የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥን ዒላማ በማድረግ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

አሊ ሻድማኒ በዚህ ወር መጀመሪያ እስራኤል የጥቃት ኦፕሬሽን ውስጥ የተገደሉትን የቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አላም አሊ ራሺድን ተክተው ሚናውን መረከባቸው ይታወሳል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ግድያው በኢራን ወታደራዊ እዝ መዋቅር ላይ ወሳኝ ጉዳትን የሚያደርስ ሲሆን፤ የኢራንን የጦር ኃይሎች ከፍተኛ አመራሮችን እስራኤል በተደጋጋሚ ዒላማ አድርጋ እያጠቃች ትገኛለች።

ኢቢሲ