“የኢራንን ሉዓላዊነት እስከመጨረሻው እስትንፋሳችን እናስጠብቃለን!” – የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም
ማሻ ፣ የሰኔ 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) “ለሀገራቸው ነብሳቸውን ከማይሰስቱ ጀግና ወታደሮቻችን ጋር በመሆን የኢራንን ሉዓላዊነት እስከመጨረሻው እስትንፋሳችን እናስጠብቃለን” ሲሉ የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጀር ጄነራል አሚር ሃታሚ ገለፁ።
የቀድሞ የኢራን ወታደራዊ መኮንን የነበሩት ሜጀር ጄነራል አሚር ለተሰየሙበት ኃላፊነት ዝግጁ መሆናቸውንም ባጋሩት መልዕክት ገልፀዋል።
ከቀናት በፊት በእስራኤል ጥቃት ሕይወታቸው ባለፈው አመራሮች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘንም ገልፀዋል።
ለጥቃቱ አመርቂ የሆነ የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት ለሚወሰዱ እርምጃዎች ቁርጠኛ መሆናቸውንም ነው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የተናገሩት።
አክለውም የጦር ሠራዊቱ የሚጠበቅበትን በሟሟላት የውጊያ አቅሙን ለማጠናከር እንደሚሰራ መጥቀሳቸውን የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
4ኛ ቀኑን በያዘው የሁለቱ ሀገራት ግጭት በሁለቱም አካላት በኩል የሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የመሰረተ ልማት ውድመቶችም ደርሰዋል።
ኢቢሲ
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ