ማሻ ፣ የግንቦት 19፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ከሚዲያ ኔትወርኩ ዘርፎች አንዱ የኾነው የድህረገጽና ማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ የሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ እና የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
የክልሉ መንግሥት ከምሥረታው ጀምሮ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ግንባታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑንና በዚህም አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የገለጹትየክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪና የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ፍቅሬ አማን ሚዲያ መንግሥትና ህዝብ መካከል እንደ ድልድይ ሆኖ በማገልገል እና አዎንታዊ ሠላምን በማጽናት ረገድ የጎላ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
ሚዲያ ኔትወርኩ በድህረ ገፅ የመረጃ ልውውጥ በተገቢው በመረዳት ለሠላም፣ የልማትና የህዝቦች የአብሮነት ዕሴቶችን ከማጎልበት ባሻገር የክልሉ ፀጋ ለተቀረው ዓለም የማስተዋወቅ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ጠቁመዋል።
የክልሉ መንግሥት ለሚዲያ ኔትወርክ መጠናከር የጀመረውን ድጋፍ በቁርጠኝነት አጠናክረው እንደሚቀጥል የተናገሩት አቶ ፍቅር ሚዲያው በምሥረታ ላይ ያለው በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ሚዲያውን እንዲደግፉት ጥሪ አቅርቧል።
ሚዲያ ገዢና አስተሳሳሪ ትርክት በመገንባት ለክልላዊና ሀገራዊ አንድነትን መጎልበት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት የሚዲያ ኔትወርኩ ስራ-አስኪያጅ አቶ መንግሥቱ መኩሪያ ፈጣን፣ ተዓማኒና ወቅታዊ መረጃ ለክልሉ ህዝብ ለማድረስ ሚዲያ ኔትወርኩ ወደ ተግባር መግባቱን ጠቁመዋል።
የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በማጠናከር 2018 በጀት ዓመት በተቋሙ ቴክኖሎጂ የማሟላት ተግባር በማከናወን ወደ ሙከራ ስርጭት ለመግባት በትጋት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ መንግስቱ ለሚዲያ ሁለንተናዊ ዕድገት ሁሉ የአምባሳደርነት ሚናውን መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ መንግሥቱ በእስካሁኑ የተቋሙ ጉዞ እና ወደ ተግባር መግባት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
በሚዲያ ኔትወርኩ ምክትል ስራ-አስኪያጅ ካሳሁን ወዳጆ (ዶ/ር) የሚዲያ ተቋሙ የእስካሁኑ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።
ክልል ኮሚኒኬሽን
More Stories
የማህበራዊ ሚዲያው ተፅዕኖ የጎላበት ምህዳር ተፈጥሯል- የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ።
የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ተልዕኮቸውን በሀላፍነት እና በዕውቀት እንዲወጡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ።
ይህ ስማርት የኮሙኒኬሽን ማሳለጫ ክፍሎች ቀልጣፋ እና ውጤታማ የስራ ተግባቦት እንዲፈጠር የሚያስችሉ ናቸው-ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)