ማሻ ፣ የግንቦት 18፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከWebuild Group ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር በሮም ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህብራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከWebuild Group ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፔይትሮ ሳሊኒ ጋር በሮም ተገናኝተን እየተሳተፉባቸው ባሉ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ተወያይተናል ብለዋል።
አያይዘውም በጥቂት ወራት ውስጥ በሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት በሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ እንዲሁም በኮይሻ ግድብ ፈጣን አፈፃፀም እንደታየው ሀገራዊ ግቦቻችንን በማሳካት ረገድ ከWebuild Group ጋር ያለን ትብብር ወሳኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ውይይታችን በመሠራት ላይ ባሉት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ በፍጥነት በታገዘ ውጤታማነት ላይ ፈጠራን እና ዘላቂነትን የሥራዎቻችን ማዕከል አድርገን መያዝ እንደሚገባ ተነጋግረናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ውይይታችን የኢኮኖሚ እድገትን በመምራት እና የረጅም ጊዜ ልማትን በመደገፍ ሀገር የሚያሻግሩ ፕሮጀክቶችን በመከወን ረገድ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ያንፀባረቀ ነበር ሲሉም አክለዋል።
ኢቢሲ
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ