May 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በጥናት ምርምር የተደገፍ ማህበረሰብ ተኮር ተግባራትን ከመፈፀም ባሻገር በጥሩ ስነ ምግባርና እወቀት የታነፁ ትውልድን ከመቅረፅ አኳያ የዩንቨርስቲ መምህራኖች ሚና የጎላ እንደሆነ ተገለፀ።

ማሻ ፣ የግንቦት 15፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ‹‹ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል፣ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ቃል ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ መምህራን ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።

በዚህ መድረክ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገብረማርያም በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት የከፍተኛ ትምህርት ተቋመት ትውልዱ በጥሩ ስነ ምግባርና በእውቀት ታንፀው ለሀገር መንግሥት ግንባታ ህደት ውስጥ የድርሻቸውን እንድወጡ ከማድረግ አንፃር ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል ።

ከለውጡ ወድህ የተለያዩ ችግሮችን በማለፍ በብልፅግና እሳቤ ዘርፈ ብዙ ድሎች እየተመዘገቡ ይገኛል ያሉት የቢሮ ኃላፊዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ድሎችን ለማስቀጠል በምደረገው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እንድወጡ ነው የተናገሩት ።

በመድረኩ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የቴፒ ካምፓስ ስራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ ከተማ ‹‹ትውልድ በመምህራን ይቀረፃል፣ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል የሚል የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት በመማር ማስተማር ህደት ያሉትን ችግሮች ለይቶ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ከማስቀመጥ አኳያ ትኩረት ልደረግ እንደምገባ ገልፀዋል ።

በመድረኩ የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢንጅነር አስራት ገብረማርያም ፣የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ካምፓስ ስራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ ከተማን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎችና መምህራኖች ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ አስቻለው አየለ