ማሻ ፣ የግንቦት 15፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የብልጽግና ጉዞና የነጋዴዉ ማህበረሰብ ሚና በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ዞን አቀፍ ምክክር ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ተካሂዷል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ግንባታ ህደት ዉስጥ የነጋዴዉ ማህበረሰብ ሚና ጉልህ መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘዉ ለማንኛዉ ልማት መረጋገጥና ዘላቂ ሰላም አይተከ ሚና ስላለዉ አሁን በዞኑ ያለዉን ሰላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ነጋዴዉ ማህበረሰብ የድርሻዉን አንዲወጣ አሰሳስበዋል።
በመድረኩም በሀገሪቱ ለዉጡን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን በተመዘገቡ ስኬቶችና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ነጋዴዎችን ለመፍጠር የሚያስችሉና መሰል ጉዳዮች ላይ በሸካ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ተግባሩ አንደሻ የዉይይት መነሻ ሰነድ እየቀረበ ሲሆን ነጋዴዎቹም መክረዉ የጋራ አቅጣጫ እንደሚያስቀሚጡ ይጠበቃል።
ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ
More Stories
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል
በክልሉ ተደራሽነቱና ፍትሃዊቱ የተረጋገጠ የፍትሕ እና የዳኝነት ሥርዓት እንዲሰፊን የተጀመረው የትራንስፎርሜሽን ሥራዎች መጠናከር አለባቸዉ፦ክብርት ወ/ሮ ሃና አረአያስላሴ