ማሻ ፣ የግንቦት 11፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት፤ የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በውይይቱ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ፣ የምክክር ሂደቱ ወደ ዋናው ምዕራፍ እየተሻገረ መሆኑን ገልፀዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎች ክልሎች ተደርጎ፤ አሁን ላይ ወደ ዋናው የማዕከል ምክክር የሚደረግበት ጊዜ ተቃርቧል ብለዋል።
ይህንን የኮሚሽኑን ተግባር እንደ ዲጂታል ሚዲያ ባለሙያ እና እንደ ሂደቱ ተሳታፊ፤ መረጃ ተደራሽ እንዲሆን በኃላፊነት መስራት እንደሚገባ የገለፁት ደግሞ ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) ናቸው።
ይህ ሂደት ከግጭት ወደ ንግግር ከንግግር ወደ ሰላም የሚመራን በመሆኑ፤ ለሰላም የዲጂታል ሚዲያ ተፅዕኖ በጎ እንዲሆን አበክሮ መስራ ያስፈልጋል ብለዋል ኮሚሽነሩ።
ከሚያገፋፉን ትርክቶች በላይ አንድ የሚያደርጉን እና ሀገራዊ ምክክሩን በማጉላት፤ ማህበራዊ ሚዲያው ግጭት የማይጠመቅበት እንዲሆን ሊሰራ ይገባልም ነው ያሉት።
ኮሚሽነሩ አክለውም ዲጂታል ሚዲያ በዚህ ጊዜ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆኑ፤ የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት ያላቸው ሚና ትልቅ እንደሆነ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በቀጣይ ከትግራይ ክልል፣ ከዳይስፖራው ማህበረሰብ እና በፌደራል ደረጃ የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራዎችን እንደሚያከናውን ተገልጿል።
ኢቢሲ
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።