ማሻ ፣ የግንቦት 10፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 34 ሺህ 258 ህጻናት የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ክልሉ በማህበረሰቡ እገዛ የትምህርት ቤቶች ምገባ ዘንድሮ መጀመሩን የቢሮው ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
በዚህም በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ልዩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
በ278 ትምህርት ቤቶች 34 ሺህ 258 ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው÷ መርሐ ግብሩ ከማህበረሰቡ በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ሀብት በመሰብሰብ የሚፈጸም ነው ብለዋል።
በቀጣይም በልዩ ሁኔታ ማህበረሰቡን፣ ባለሃብቱን እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማሳተፍ የምገባ መርሐ ግብሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ መሆኑን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
More Stories
በሸካ ዞን ማሻ ወረዳ የበልግ የአረንጓዴ አሻራ በወረዳ ደረጃ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄዷል ።
በ2017 ዓ/ም አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ ከ399 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ ይካሄዳል፦ አቶ ማስረሻ በላቸው
በበጋ መስኖ ከ66 ሚሊየን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ተሰበሰበ