May 5, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዌኖ እንኳን ለ116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ምሥረታ ቀን በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

ማሻ ፣ የሚያዝያ 26፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዌና ለመላዉ የፖሊስ አመራሮችና አባላት ለ116ኛዉ የኢትዮጵያ ፖሊስ ምሥረታ ቀን በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን በማለት ለመላዉ የክልሉ ፖሊስ አመራሮችና አባላት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

የምሥረታ በዓሉ “ያደገ ፖሊስ እየተለወጠ ላለ ሀገር” በሚል መሪ ቃል የሚከበረዉ የፖሊስ ቀን ሀገራችን እያስመዘገበች ለምትገኘዉ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ፖሊስ የሰላም ዘብ በመሆን የድርሻዉን መወጣቱን ነዉ ኮምሽነር ሰብስቤ የገለፁት።

ዛሬም እንደትላንቱ ፖሊስ የህዝብ ወገንተኝነቱን በማጠናከር በወንጀል መከላከል፣በምርመራ እና በትራፊክ አደጋ ቁጥጥር ህዝብ በማሳተፍ ይበልጥ ለመስራት ይተጋል ብለዋል።

በተለያዩ አከባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ተሰማርታችሁ ለምትገኙ ለመደበኛ ፖሊስ ፣ለአድማ ብተና እና ለከፍተኛ ባለስልጣናትና ተቋማት ጥበቃ እና የፈደራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ለመላዉ የፖሊስ አጋርና ለህዝቡ እንኳን ለ116ኛዉ የፖሊስ ምስረታ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ሲሉ መልክታቸዉን አስተላልፈዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘግቧል።