May 3, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከልና ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ተባለ ።

ማሻ ፣ የሚያዝያ 24፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም)በቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ ያሉትን ችግሮች በመፍታት ውጤታማ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የግምገማ መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሂዷል ።

በዚህ መድረክ ላይ የሸካ ዞን ጤና መምርያ ሀላፊ አቶ እምሩ ወዬሳ እንደገለፁት የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገቢውን የጤና አገልግሎት እንዳይሰጥ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን ለመለየት ከተቋሙ ስራተኞች ጋር ጥልቅ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል ።

በዚህም ችግሮች ተለይቷል ያሉት አቶ እምሩ የሆስፒታሉ አስተዳደር ሰራተኞችና ባለሙያዎች በተጠያቂነት ተገቢውን አገልግሎት ለተገልጋዩ ማህበረሰብ መስጠት እንዳለባቸው ገልፀዋል ።

የሸካ ዞን ምክትል አስተዳደርና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ በላቸው ጋራ በበኩላቸው ተገልጋዩ ማህበረሰብ በቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ የሚያነሷቸው ቅረታዎች የመልካም አሰተዳደር ስራዎችን ችግር ውስጥ እያስገባ ይገኛል ብለዋል።

ቀጣይ ሆስፒታሉ ከገባበት ችግር እንድወጣና የተሟላ የጤና አገልግሎት መስጠት እንድችል ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እንደምሰራ ገልፀዋል ።

በመድረኩ ላይ ከተሳተፍ አካላት አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት የጤና ፓሊሲን መሰረት ያደረጉ የህክምና አግልግሎቶችን ከመስጠት በተጨማሪ የሙያውን መርህ በመከተል ለተገልጋዩን ማህበረሰብ የተቋሙ ሰራተኞች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል ።