ማሻ ፣ የመጋቢት 24፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ይህን የገለፁት የሸካ ዞን ልዩ የአዳሪ ትምህርት ማስጀመሪያ መረሃ ግብር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።
የመመዘኛ ፈተና አልፈው በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ልዩ አዳር ትምህርት ለመማር ከመጡት ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደገለፁት ይህ አድል መፈጠሩ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ተወዳዳሪ እንድሆኑ እንደሚያግዛቸው ነው ።
ትኩረታችን በተሻለ እውቀት ወደ ተሻለ ደረጃ መድረስ ነው ያሉት ተማሪዎቹ አሁንሥ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል ስራዎችን እንድያጠናክሩ ጠይቀዋል ።
የተማሪ ወላጆችም በበኩላቸው የዞን መንግሥትና በየደረጃው የሚገኙ አካላት ይህን እድል በማመቻቸቱ አመስግነው ልጆቻቸውን በተለየ መልኩ ክትትል እንደሚያደርጉ ገልጸዋል ።
ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለማፍራት የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ ተናግረው የዘርፉን ስራ ለመደገፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ጠቁመዋል ።
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።