በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “ለዓመታት ተንሰራፍቶ የነበረው” የሰራተኞች የውስጥ ችግር በውይይት መፈታቱ ተገልጿል፡፡
አለመግባባቱ የተፈታው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከሠራተኞች ጋር ባደረጉት “ግልፅ” ውይይት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን አስመልክቶ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት ፤ ፌዴሬሽኑ “ለዓመታት ተከማችቶ የነበረውን የሠራተኞች አለመግባባት ችግር በውይይት ሙሉ በሙሉ በመፍታት ደማቅ ታሪክ ፅፏል” ብሏል፡፡
በመድረኩ በየሥራ ሂደቱ የተከናወኑ ተግባራት ተገምግመው የ100 ቀናት የሥራ ዕቅድ ላይ ውይይት መደረጉም ተመላክቷል፡፡
More Stories
ትዕግስት አሰፋ በዓለም አቀፉ የድንቃ ድንቅ መዝገብ እውቅና ተሰጣት
ኢትዮጵያ በፊፋ ደረጃ 147ኛ ሆናለች
ኬቨን ዲብሮይን በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ተረጋገጠ