ማሻ፡ ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ ማሻ ቅርንጫፍ) ወቅቱን ሊመጥን የሚችልና በየጊዜው እያደገ በሚሄደው የዘርፉ ውድድር በብቃት መሳተፍ የሚችል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስርኣት ግንባታ ጠንካራ ቅንጅትና መናበብን ይጠይቃል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪና የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ተናግረዋል።
ዶ/ር ዲላሞ ከክልሉ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮች ጋር በዘርፉ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ እየተወያዩ ሲሆን በዚሁ ወቅት እንዳሉት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎች ወቅቱን የሚመጥኑ እንዲሆኑ ዘላቂና ጠንካራ የአመራር ቅንጅትን ይጠይቃሉ።
ከዚህ መነሻ እውነትን መሰረት ያደረጉ መረጃዎችን ለህዝብ በወቅቱ ተደራሽ ማድረግና በህብረተሰቡ ውስጥ የመጣውን አዎንታዊ ለውጥ በየጊዜው ለመገምገም የሚያስችል የሚዲያ አመራር ስርዓት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።
የክልሉ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሰብስቤ ተካ ባቀረቡት የውይይት ሰነድ በበኩላቸው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎች የመረጃ የበላይነትን ሊያረጋግጡ የሚችሉ፣ ገዢ ትርክትን የሚያሰርጹና ሀገራዊ የለውጥ ራዕይን መሰረት ያደረጉ መሆን አለባቸው ብለዋል።
በውይይቱ የመንግስትና የፓርቲ የሚዲያ ዘርፍ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ሲሆን የክልሉ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ ደሬቴድ
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …