የ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክብረ በዓል አካል የሆነው የዋዜማው የእራት መርሐ-ግብር በጋሞ ምርምር እና ባህል ማዕከል አዳራሽ እየተካሄደ ነው።በመርሐ-ግብሩ ግብሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ለገሰ ጫፎ፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምሕረት፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች እንዲሁም የ76ቱ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ተወካዮችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።በመርሐ-ግብሩ ለበዓሉ በድምቀት መዘጋጀት የላቀ አፈፃፀም ላላቸው ክልሎች እና አመራሮች በፌዴሬሽን ምክር ቤት እና በአዘጋጁ ክልል አማካኝነት የምስጋና እና የእውቅና ሽልማት ይሰጣል።
EBC
More Stories
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።
ኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ …