በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል አቻ ተለያይተዋል፡፡ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ በተደረገው ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በዮስኮ ጋቫርዲዮል ጎል ቀዳሚ መሆን ቢችልም ከእረፍት መልስ አንቶኒ ጎርደን ፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ጎል ቀይሮ ባለሜዳዎቹን አቻ አድርጓል፡፡ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ፕሪሚየርሊጉን በ14 ነጥብ በጊዜያዊነት መምራት ሲችል ኒውካስል ነጥቡን ወደ 11 ከፍ በማድረግ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡የሊጉ 6ኛ ሳምንት መርሃግብሮች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ አርሰናል ከሌስተር ሲቲ፣ብረንትፎርድ ከዌስትሃም፣ቼልሲ ከብራይተን፣ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ፣ኖቲንገሃም ፎረስት ከፉልሃም እንዲሁም ወልቭስ ከሊቨርፑል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ
More Stories
የ2026 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ …
እንግሊዝን ያስቆጣው የኢራን ጥቃት
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐግብር የተሠማሩ ወጣቶች ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣቸው ተገለጸ።