የዩክሬን ወታደሮች በሩሲያ ግዛት ዘልቀው በመግባት እየተዋጉ መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ገለጹ፡፡
ዘሌንስኪ ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደራቸው በሩሲያ ምዕራባዊ ኩርስክ ግዛት ድንበር ውጊያ ላይ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን ፥ ጥቃት እያደረሰ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
ዩክሬን ድንገተኛ ጥቃቱን የጀመረችው ባሳለፍነው ማክሰኞ ዕለት መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አመልክተዋል፡፡
በዚህም የሀገሪቱ ወታደሮች በፍጥነት ወደ ሩሲያ ከ10 ኪሜ በላይ መግባታቸው ነው የተገለጸው፡፡
የዩክሬን ወደ ሩሲያ ግዛት በድንገት ዘልቆ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ መገለጹንም ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
ይህን ተከትሎም በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ እና ሌሎች በርካታ ግዛቶች ከሰዓታት በፊት ሩሲያ በድሮን እና በሚሳኤል ጥቃት መፈጸሟ ተሰምቷል፡፡
FBC
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ