ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበል ብቻ ሳይሆን የሚኖሩበትን ቦታ እንዲንከባከቡ በማድረግ ረገድም ትልቅ ተሞክሮ እያሳየች መሆኗን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች፣ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች በጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡በዚሁ ወቅት በችግኝ ተከላው የተሳተፉ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማትና ግለሰቦችን ያደነቁት አቶ ተመስገን÷ የዛሬው መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ታኅሣስ 2023 በጀኔቫ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ኮንፈረንስ ላይ ቃል የገባችው የ100 ሚሊየን ችግኝ በአራት ዓመት የመትከል ግብ ማስጀመሪያ ነው ብለዋል፡፡ኢትዮጵያ በጀኔቫ ቃል የገባችውን ከተቀመጠው ዓመት ባነሰ ጊዜ እንደምታጠናቅቅም አመላክተዋል፡፡የዛሬውን የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ያስተባበረው የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን በበኩላቸው÷ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነቱን በመተግበር ሥራው የአረንጓዴ ዐሻራ ተሳትፎ አንዱ አካል ሆኖ እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብርም ተቋሙ በመላ ሀገሪቱ 5 ሚሊየን ችግኞችን ይተክላል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስደተኞች ያሉበትን ቦታ እንዲንከባከቡ በማድረግ ትልቅ ተሞክሮ እያሳየች ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን

More Stories
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል የገባ ስንዴ የለም – አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
በገጠሩ የሀገሪቱ አካባቢዎች መንግስት የሚዘረጋቸውን የተለያዩ ኢንሸቲቦችን ቀድሞና ፈጥኖ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የተሻሉ አፈጻጸሞች መታየታቸው ተገለፀ ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ6 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ