አርባን ትራምፕ ዩክሬን እና ሩሲያን ማደራደር እንደሚፈልጉ ለአውሮፓ መሪዎች የተናገሩት በዋሽንግተን ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ነውትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ ወዲያውኑ ሩሲያ እና ዩክሬንን ወደማደራደር እንደሚገቡ ኦርባን ለአውሮፓ ህብረት በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል።የሪፐብሊካኑ እጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በመጭው ህዳር የሚካሄደውን ምርጫ የሚያሸንፉ ከሆነ ሩሲያ እና ዩክሬንን ወዲያውኑ ወደማደራደር እንደሚገቡ የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክተር ኦርባን በጽሁፍ ለአውሮፓ መሪዎች ነግረዋቸዋል ተብሏል።ለአውሮፓ ህብረት ካውንስል ምክርቤት ፕሬዝደንት ቻርለስ ሚሸል እና ለሁሉም መሪዎች የተጋራው ይህ ደብዳቤ የተጻፈው፣ ኦርባን ከትራምፕ ጋር ካወሩ እና እንዲሁም ዩክሬንን፣ ሩሲያን እና ቻይናን ከጎበኙ በኋላ ነው።
Al-Ain
More Stories
ትራምፕ ቲክ ቶክን የሚገዙ የአሜሪካ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን ገለፁ
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ