ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ስልጠና በዛሬው ዕለት በመደመር ትውልድ እና የውጭ ግንኙነት ፓሊሲ አንኳር መርሆዎች ላይ አተኩሮ ተካሂዷል። በመደመር መንገድ በውጭ ግንኙነት ስራዎች ባለፉት አመታት በተገኙ ስኬቶች እና የተግባር ለውጦች ዙሪያ ለአምባሳደሮቹ ገለፃ ተደርጓል። መደመር አገር በቀል እሳቤ መሆኑን በመገንዘብ በዲፕሎማሲው መስክ ሃገራዊ ክብርን እና ጥቅምን ለማስጠበቅ በትጋት ሊሰራ እንደሚገባም በመድረኩ ተነስቷል። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፓሊሲ ዓለምአቀፍ አሰላለፍን በመገንዘብ ከፉክክር ይልቅ ትብብርን በማስቀደም መሰረታዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የሚያስችል መሆኑ ተብራርቷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ መድረኩን በአወያይነት መምራታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
EBC
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።