የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 54 ሺህ 795 ሜትሪክ ቶን የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡
አጠቃላይ አቅርቦቱም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃርም የ28 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ነው የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያስታወቁት፡፡
እየተሻሻለ የመጣው የቡና ማሳ እንክብካቤ፣ በክልሉ የቡና ቅምሻና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል ሥራ መጀመር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር መጠናከር እንዲሁም በግብይት ሂደት ያጋጥሙ የነበሩ ማነቆዎችን መፍታት መቻሉ ለምርት ዕድገቱ አስተዋፅኦ ማበርከቱንም አብራርተዋል፡፡
በ2017 የበጀት ዓመትም ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ በተሻለ አቅም እና ተነሳሽነት መሥራት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡
FBC
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።