“ከታሪካዊ መሰረትዎ ጋር ይገናኙ” በሚል መሪ ሃሳብ ወደ ሀገራቸው የመጡ የ2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የፓናል ውይይት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል። መርሀግብሩ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውን ከታሪካዊ መሰረታቸው ጋር እንዲገናኙ እና ስለሀገራቸው እንዲያውቁ ለማድረግ የተሰናዳ ነው።በመርሀግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እንዲሁም ከተለያዩ አገራት የመጡ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ “ከባህልዎ ጋር ይተዋወቁ” በሚል በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር መርሀግብር በርካታ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት መምጣታቸውን አስታውሰዋል።2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያኑ ከታሪካዊ መሰረታቸው ጋር እንዲገናኙ በተሰናዳው ሁለተኛው ዙር መርሀግብርም በርካታቶች ወደ ሀገራቸው መምጣታቸውን ተናግረዋል። የቱሪዝም ሚኒስትሯ በንግግራቸው፥ ኢትዮጵያ የሚያኮሩ በርካታ ባህሎች እንዳሏት አንስተዋል። የአዲስ አበባ ከተባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ ትልልቅ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ፤ ሀገሪቱም በለውጥ ጎዳና ላይ እየተራመደች መሆኑን አንስተዋል። ኢትዮጵያ የሚያኮራ ትልቅ ታሪክ እንዳላት የጠቀሱት ከንቲባዋ፤ ያለፉ ስህተቶች ቢኖሩ እንኳ ከመራራቅ ይልቅ ተቀራርቦ በመነጋገር በጋራ ማረም እንደሚገባ ጠቁመዋል።ለዳያስፖራ አባላቱ የኢትዮጵያን ታሪክ እና ለሀገራቸው ሊያበረክቱት የሚችሉትን አስተዋጽኦ የተመለከተ የመነሻ ገለፃ ቀርቦላቸው ተወያይተውበታል።
EBC
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።