

በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ወደ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴን ለመመልከት በስፍራው ተገኝተዋል ።
በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የምዕራብ ኦሞና ካፋ ዞን አመራሮች የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ስኳር እንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ እና የፋብሪካዉ አመራሮች አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩና ልዑካቸዉ ሁለት ቀን በሚኖራቸዉ ቆይታ የፋብሪካዉን የስራ ዕንቅስቃሴ፣የእርሻ ሁኔታ እና የምርት ሂደት እንዲሁም በምዕራብ ኦሞ ዞን እየተሰሩ ያሉ የመንገድና የኢንቨስትመት ፕሮጀክቶች በመጎብኘት በነገው ዕለት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዘገበው የክልሉ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።
More Stories
የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያሳድጋል
በክልሉ ተደራሽነቱና ፍትሃዊቱ የተረጋገጠ የፍትሕ እና የዳኝነት ሥርዓት እንዲሰፊን የተጀመረው የትራንስፎርሜሽን ሥራዎች መጠናከር አለባቸዉ፦ክብርት ወ/ሮ ሃና አረአያስላሴ