የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ለተለያዩ የልማት ስራዎች ጉብኝት አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ገብተዋል።የአፋር ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በሱልጣን ዓሊሚራህ ሀንፍሬ የአየር ማረፊያ ተገኝተው ለልዑኩ አቀባበል አድርገዋል።ልዑኩ በአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የበጋ መስኖ ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎችን እንደሚጎበኝ ተገልጿል።
FBC
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ