
በአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ የሚወሰደው የማያዳግም ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለጹ።
የሽብር ቡድኑን በመደምሰስ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከምንጩ ለማድረቅ የሚያስችል ውጤታማ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በጥናት ላይ የተመሰረቱ በርካታ ዘመቻዎችን በማድረግ የአሸባሪ ቡድኑን አባላት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን እና በቡድኑ ታጣቂዎች ላይ የሚወሰደው የማያዳግም ርምጃም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በተከናወኑ ሕግ የማስከበር ሥራዎች ሠላም እንዲረጋገጥ ማድረግ ተችሏል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
FBC
More Stories
ሮቦቶችም ተማሪ ሆኑ! በቻይና የተከፈተው የዓለማችን መጀመሪያው የሮቦቶች ትምህርት ቤት አስገራሚ እውነታ
የግል ጄታቸውን ለሕዝብ አምቡላንስ አገልግሎት የለገሱት ጋናዊው ቱጃር
ፌራሪ የመጀመሪያውን ባለ 5 መቀመጫ የኤሌክትሪክ መኪና አስተዋወቀ