
በቅርብ የሚመረቁት የጎርጎራ ፕሮጀክት እና የዓባይ ድልድይ ለሕዝብ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድል እንደሚያስገኙ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ማሥተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ ከአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጋር በመሆን÷ የዓባይ ወንዝ ድልድይን ጨምሮ የተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እና የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ ተመስገን በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ በባሕር ዳር ከተማ የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ከአካባቢው ሕዝብ በተጨማሪ ለሀገርም ትልቅ ጸጋ ናቸው።
የጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እና ውብ የሆነው የዓባይ ድልድይ በቅርቡ እንደሚመረቁ ጠቁመው÷ ለባሕር ዳር ሕዝብ ብሎም ለሀገር ትልቅ የቱሪዝም ትሩፋት እንደሚያስገኙ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ሕዝቡ ሰላም እና ልማት እንደሚፈልግ ገልጸው÷ ተገንብተው ከተጠናቀቁ እና ገና ከሚጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠቃሚ ለመሆን የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እና ማጽናት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ችግሮች ቢከሰቱ እና ጥያቄዎች ቢኖሩ እንኳን በሰለጠነ አግባብ እየተወያዩ የመፍታት ባህልን ማዳበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
FBC
More Stories
መንግስት በፈጠራና ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ሀገራዊ የጤና ፖሊሲ ከመከላከልባሻገር አክሞ መዳንን መሰረት ያደረገ ስራን መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኢራን ወደብ በደረሰ ፍንዳታ 25 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ