አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በማሳደግ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላምን የሚያመጣ ነው አሉ ምሁራን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁንና በመጪው መስከረም ወር እንደሚመረቅ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
የግድቡ መጠናቀቅ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን በማሳደግ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላምን የሚያመጣ መሆኑን ነው የፖለቲካና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን የሚገልጹት፡፡
የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኙ ሴኔሳ ደምሴ እንደሚሉት፥ የህዳሴው ግድብ ከፍ ያለ ኃይል የያዘ በመሆኑ ሰጥቶ የመቀበል አለምአቀፍ የዲፕሎማሲ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም በር ከፋች ይሆናል።
አንዱ የሌለውን ከሌላው ጋር እንዲጋራው በማድረግ ምጣኔ ሀብታዊ ትስስርን በማሳደግ ቀጣናውን ወደ ሰላም የማምጣት ዕድል እንዳለው አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴ በበኩላቸው፥ የግድቡ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን ተጽዕኖ ከነበረበት ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ ለምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ከፍ ያለ ጥቅም ይዞ እንደሚመጣ ነው የተናገሩት።
በክብረወሰን ኑሩ
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።