August 21, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ምክር ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር እየተወያየ ነው

ማሻ ፣ የሰኔ 24፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) 6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 41ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በስብሰባው በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር እየተወያየ ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴሩ አሕመድ ሽዴ ከምክር ቤቱ አባላት የቀረቡ ጥያቄ እየተቀበሉ ሲሆን፤ የምክር ቤቱ አባላት የበጀት አቅርቦቱ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ምን ያክል በቂ ነው የሚል ጥያቄ አቅርበዋል።

የበጀት ድልድሉ ፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የሕዝብና የቤት ቆጠራ መደረግ እንዳለበት ተነስቷል።

በክልል የተለያዩ አካባቢዎች የመንገድና ጥገናና ፕሮጀክቶች ግንባታ ሊደረግ ይገባል የሚሉና የክልሎች የበጀት ድጎማ ከፍ ማለት አለበት የሚሉ ጥያቄዎችም ቀርበዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ኢቢሲ