August 21, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የአውራዳ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው ከፈቱ

ማሻ ፣ የሰኔ 24፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በካፋ ዞን አውራዳ ከተማ አስተዳደር የተገነባውን የአውራዳ ኮንስተትራክሽ እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው ከፍተዋል።

ሙሉ በሙሉ የግንባታ ወጪው በክልሉ መንግሥት የተሸፈነው ኢንዱስትሪያል ኮሌጁ በውስጡ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ፥ ባሌ 2 ፎቅ የአስተደዳደር ህንፃ፤ባሌ 1 ፎቅ የመማርያ ክፍል፤ላይቢራር ፤1 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፤2 መጸዳጃ ቤቶች ወዘተ ያካተቴ ስሆን ግንባታዉን አሁን ባለዉ ደረጃ ለማጠናቀቅ 53 ሚሊዮን 845ሺህ 246 ብር ወጪ እንደወጣበት ነው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዐቢይ አንደሞ (ዶ/ር) የገለጹት።

በምረቃው ስነስርዓት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፣ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደን ጨምሮ የክልል እና የካፋ ዞን እንዲሁም የአውራዳ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ክልል ኮሚኒኬሽን