ማሻ ፣ የሰኔ 19፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) “ጋዜጠኛ ወገን የለውም፤ ሃይማኖት የለውም፤ የሚደግፈው ፖለቲካ የለውም …” የሚሉ የጋዜጠኝነት መርሆች አሉ፡፡
እነዚህ መርሆች ግን ምንድን ናቸው? ለመሆኑ ጋዜጠኛ በእነዚህ መርሆች ሲመራ ዜግነቱን ያጣል? ይህ ጉዳይ ከብሔራዊ ጥቅም ጋርስ እንዴት ይናበባል?
የዚህ ሀሳብ መነሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከመገናኛ ብዙኃን ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ያነሱት ጉዳይ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ “ጋዜጠኝነት ዜግነት የለውም ብላችሁ የምታስቡ ሰዎች ካላችሁ ተሳስታችኋል፤ ጋዜጠኝነት ዜግነት አለው፤ ልክ እንደወታደር፣ ልክ እንደ ሐኪም፣ ልክ እንደ መምህር፣ ልክ እንደ ደኅንነት ሠራተኛ ጋዜጠኝነት ዜግነት አለው፤ ጋዜጠኝነት ብሔራዊ ጥቅም አለው፤ ጋዜጠኝነት የሚቆምለት ሀገር እና ባህል አለው፤ …” ብለዋል፡፡
የጋዜጠኝነት ሳይንስ ውስጥ ስለ ጋዜጠኛ ዜግነት እና የጋዜጠኝነት መርሆዎች “በነቃ ማኅበረሰብ ውስጥ የጋዜጠኛ ዜግነት እና የጋዜጠኝነት መርሆዎች ሁለት ተያያዥ ግን ልዩ ልዩ ፅንሰ-ሀሳቦች ናቸው በሚል” በጥቅል ተጠቅሷል፡፡
ይህም ሲዘረዘር ጋዜጠኝነት እንደ ሙያ ለጋዜጠኛው የሚሰጣቸው መብቶች ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት፣ መረጃ የማግኘት መብት እና በነፃነት የመንቀሳቀስ መብቶችን የሚያጠቃልል ነው፡፡
እነዚህ የጋዜጠኛው መብቶች ደግሞ የሀገር ሕጎን ማክበር፣ የሀገር ብሔራዊ ጥቀምን ማስጠበቅ እና የሀገር ሰላምን የሚያደፈርሱ ድርጊቶች ላይ አለመሳተፍ ከሚሉት የዜግነት ግዴታዎች ጋር ፈጽሞ የሚጋጩ እንዳይደሉ ነው ጋዜጠኝነትን በተመለከቱ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች እና ስምምነቶች ላይ የሰፈረው፡፡
ሙሉ ምንባቡን ለማግኘት አስተያየት መስጫው ላይ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
ኢቢሲ
More Stories
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ ማሰባሰብ ጀመረ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ማህበረሰቡ በከባድ ዝናብ ምክንያት ከሚከሰቱ አደጋዎች እንዲጠነቀቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።